Yabets

Call Directions Contact the business

Yabets social service

25/07/2022

🟣✴ ✴🟣

🟢 ከልምዶች ሁሉ ጎጂ 👉👉 ጭንቀት
🟢 የሚያኮራ ስራ 👉👉 ሰወችን መርዳት
🟢 አስቀያሚ ባህሪ 👉👉 ራስ ወዳድነት
🟢 መጥፎ ልማድ 👉👉 መስረቅ
🟢 ትልቅ የተፈጥሮ ሀብት 👉👉 ወጣትነት

💠 ትልቅ መሳሪያ 👉 ብርታት
💠 መጥፎ ፀባይ 👉 ይሉኝታ
💠 ቆንጆ ጌጥ 👉 ፈገግታ
💠 አደገኛ ስብከት👉 አሉባልታ
💠 ትልቅ ስጦታ 👉 ምክር

🟣 የሰዉ ልጅ እንቆቅልሽ 👉 ኑሮ
🟣 አደገኛ መሳርያ 👉 ምላስ
🟣 ራስን የመጉዳት ዘዴ 👉 ማልቀስ
🟣 በሀይል የተሞላ ቃል 👉 እችላለሁ
🟣 ታላቅ ተስፋ 👉 እኖራለሁ

🔶 ️ዉድ ሀብት 👉 እምነት
🔶 ️ሀይለኛ የመገናኛ መሳርያ 👉 ፀሎት
🔶 ️ልንፈታዉ የሚገባን ችግር 👉 ፍርሀት
🔶 ️ዉጤታማ የእንቅልፍ ክኒን 👉 የአእምሮ እረፍት
🔶 ️መጥፎ የዉድቀት በሽታ 👉 ከስህተት ይቅርታን አለመጠየቅ
🔶 ️የህይወት ሀይለኛ ጉልበት 👉 አእምሮ
🔶 ️ከህይወት ልምዶች የምድር ታላቅ ደስታ 👉 መስጠት

🟢 🟢

🚹 ትላንት ታሪክ ነዉና ተርከዉ
🚺 ዛሬ ቁምነገር ነዉና ተጠቀምበት
🚹 ነገ ምስጢር ነዉና ድረስበት

🚺🚺 ለመነሳት ከፈለክ መዉደቅህን አምነህ ተቀበል 🚹🚹

03/06/2022

🌀✅ ወዳጄ ሆይ በዙሪያህ ሰው ያጣህ ቀን ራስህን ወዳጅ የሌለው ብቸኛ ሰው አርገህ በፍፁም እንዳትጨነቅ ፤ ሰው ብቸኛ ነው የሚባለው ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ሲርቅ ነውና ፤ ወዳጄ አንተ እንደ መፃጉ ሰው የለኝም ብለህ ተስፋ ቆርጠህ ይሆናል ግን አስተውል " አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም" ተብሎ ተፅፏል ።

ትናንት አጃቢ የበዛልህ ሰው ነበርክ ዛሬ ግን ብቻህን ቁመህ ይሆናል በዚህም ብዙ አትደነቅ ከክርስቶስ እጅ እንጀራ እና አሳ በበረከት ሲበሉ የነበሩ ሰዎች መች በመከራው ጊዜ በቀራንዮ አደባባይ ከርእሱ ጋር ቆሙ ታዲያ ሕይወት ለሰጣቸውና ምግበ ነብስ ምግበ ሥጋ ለሆነላቸው ለክርስቶስ ያልሆኑ ሰወች እንዴት ለእኔ አልሆኑም ብለህ ትገረማለህ ?

አይንህን ገልጠህ ልብህን ከፍተህ አስተውል #ሰው ማለት ሸንበቆ ነው ከተደገፍከው ይሰበራል ተሰብሮ እንኳ አይተውህም ስለተደገፍከኝ ነው የተሰበርኩት ብሎ ስባሪውን አሹሎ ውስጥህ ድረስ ይወጋሀል ፤ እናም ወዳጄ በጆሮህ ሳይሆን በልብህ ስማኝ ዘመድ ወይም ታማኝ ጓደኛ ላይኖርህ ይችላል ግን ከሁሉ በላይ ሆኖ ሁሉን የሚገዛ ኋለኛው እና መጨረሻው እኔ ነኝ ያለው አንተን ከፍ አርጎ የሚሾምህ እግዚአብሔር ስላለህ ወዳጅ አዝማድ ስለማጣትህ በፍፁም እንዳትጨነቅ ዮሴፍን ወንድሞቹ በግፍ ሸጠውት ወደ ግብፅ ሲወርድ ማንም ሰው አልነበረውም #እግዚአብሔር ግን በጲጥፋራ ቤት በባዕድ ሀገር ገዥ አድርጎ ሾሞታል ።

በዚ እኔና አንተም ባለንበት ዘመንም ዛሬም ድረስ በሰዎች ተንኮል ብዙዎች ይሸጣሉ ፣ ይገፋሉ ፣ ይሰደዳሉ እግዚአብሔር ደግሞ በፍቅሩ ገዝቶ መገፋትህን ገፍቶ በምድሩ ይሰበስብሀል እናም ወዳጄ ጊዜን አይቶ የማይከዳ ዘመን የማይለውጠው ምንጊዜም ሰው ለሌላቸው ቀድሞ የሚደርስና ስላንተ ካንተና ከሰወች በላይ የሚጨነቅልህ የነብስህ ጌታ የሆነው ዘላለማዊው እግዚአብሔር አለህና ስጋህን አይተው ለሚቀርቡህና ለሚርቁህ ስጋ ለባሽ ፈራሽ ሰወች ስለማጣትህ በጭራሽ የሰናፍጯን ቅንጣት ታክል ጭንቀት እንዳይገባህ በሱ በፈጠረህ ብቻ የሰናፍጯን ቅንጣት ታክል እመን ያኔ ብቻህን ሆነህ እልፍ ትሆናለህና።

24/05/2022

🚺 በ4 ቀን ውስጥ ጥርስን ለማንጣት የሚጠቅም 🚺

በተፈጥሮአዊ መንገድ ህክምና ድረስ መሄድ ሳያስፈልገን ቤታችን ውስጥ ጥርሳችን እንዴት ማንጣት እንችላለን? በተፈጥሮአዊ መንገድ ዘውትር በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ትመለከታለህ...!!
እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን?

🌀መጠን...!!

1. ለብ ያለ ውሃ ሁለት ብርጭቆ!!

2. የተፈጨ ቀረፋ አንድ ማንኪያ!!

3. የንብ ማር አንድ ማንኪያ!!

4. የሎሚ ጠብታዎች!!

🌀አዘገጃጀት...!!

ትንሽ ተለቅ ባለ ብርጭቆ ውሃውን እንጨምራለን...!!ከዚያም ቀረፋውን እና ማሩን እናስከትላለን!! በመጨረሻም ከአምስት የማይበልጡ የሎሚ ጠብታዎችን እንጨምርበትና በደንብ አዋህደን ስናበቃ ዘውትር ጠዋት አፋችንን እንጉመጠመጥበታለን...!! ለውጡን በ4 ቀናት ውስጥ ቁልጭ አድርጎ ያሳይወታል...!!

በካትሪን ኩልማን ፕሮግራም ላይቤን ሂን ላይ በሀይል የተገለጠው የመንፈስ ቅዱስ ክብርሐሙስ  ለሊት የቶሮንቶን ከተማ ለቀን ወጣን። ሰባት ሰዓት የሚፈጀው የአውቶቡስ ጉዟችን ግን ባልታሰበ የበረ...
24/05/2022

በካትሪን ኩልማን ፕሮግራም ላይ
ቤን ሂን ላይ በሀይል የተገለጠው የመንፈስ ቅዱስ ክብር

ሐሙስ ለሊት የቶሮንቶን ከተማ ለቀን ወጣን። ሰባት ሰዓት የሚፈጀው የአውቶቡስ ጉዟችን ግን ባልታሰበ የበረዶ ዝናብ ፒትስበርግ ለመድረስ ብዙ ጊዜ ወሰደብን። ባሰብነው ሰዓት ወደ ሆቴላችን መድረስ አልቻልንም። እንደምንም ብለን መድረስ አይቀርምና መሀል የፒትሰበርግ ከተማ በሰላም ገባን። የውጪው ብርድ የዋዛ እንዳይመስላቸሁ። ወፍራም የእጅ ጓንት አጥልቀን፣ ከባድ የብርድ ጃኬት ደራርበን ሰሜን ዋልታ የሚገኙት ስኪሞዎችን መስለን ነበር። አረፋፍደንም ቢሆን የፒስትስበርግ ፕሪስባይቴሪያን ቤተክርስቲያን ደረስን። የሚገርመው እኩለ ቀን እየተቃረበ ነበር። የክረምቱ ጨለማ ግን አሁንም ከከተማዋ አየር ላይ አልተገፈፈም።የገረመኝ ጉዳይ ቢኖር ከቤተክርስቲያኒቱ አዳራሽ ውጪ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሰዎች እየተጋፉ ነበር። የቤተክርስቲያኒቱ በር እስኪከፈት ድረስ በዛ ጫን ያለ የውርጭ ከባቢ አየር ውስጥ ለሁለት ሠዓታት ያህል መቆማችን ግድ ነበር። ለጋ ዕድሜዬንና ትንሹ ሰውነቴን ተጠቅሜ ሾላልኬም ቢሆን ወደ ቤተክርስቲያኒቱ ዋና መግቢያ በር ደረስሁ። የወዳጄን ጂም እጅ ከኋላዬ እየጎተትሁ። አንዳንድ ሰዎች ለሊት ወደዛ ስፍራ መጥተው ስለነበር በእንቅልፍ እጦት ምክንያት በየደረጃው ተኝተዋል። አንዲት ሴት አጠገቤ የነበረች «ለሊቱን ሙሉ እዚህ ነበሩ፣ በየሳምንቱ ይህ ነገር የተለመደ ነው» ብላ አንሾካሾከቺልኝ።
እዛው ቆሜ ሳለሁ እንግዳ ነገር በሰውነቴ ላይ ይሆን ጀመር። ድንገት ሰውነቴ ወባ እንደያዘው ሰው መርገፍገፍ ጀመረ። በአይህምሮዬ ውስጥ ለዚህ ምክንያት መስጠት ጀመርኩኝ። «አይ ምናልባት ቀዝቃው አየር ይሆናል» አልኩኝ። ልክ አንድ ሰው በሁለት እጆቹ ሰውነታችሁን ጨምቆ ወዳላይ ከፍ አድርጓችሁ እንደሚወዘዋችሁ ዓይነት ያለ ስሜት። ዳሩ ግን ልብሴን በሚገባ ለብሻለው። ለዛው ብርዱን ተቋቁሞ ሙቀት በሚገባ የሚሰጥ ልብስ። ልቆጣጠረው የማልችለው አንቀጥቅጥ ኃይል በድንገት ሰውነቴን ያርደው ጀመረ። ከዚህ በፊት ሰውነቴ እንዲህ ሆኖ እንደማያውቅ እርግጠኛ ነበርሁ። ማቆም አልቻልኩም። ልቋቋመውም ጭምር። ይባስ ብሎ አጥንቶቼም ሲንዘፈፉ ተሰማኝ። በተለይ የእግሮቼ ጉልበት ላይ ። በአንደበቴ በለዖሳስ «ምን ሆንኩኝ?» አልኩ። ደነቀኝ። ገረመኝም። «የእግዚአብሔር ኃይል የሚባለው ይሄ ይሆን?» ብዬ አሰብኩኝ። ብቻ እየሆነብኝ ያለው ነገር ድብልቅ ሀሳብና ስሜት ፈጠረብኝ።የቤተክርስቲያኑ በር ልክ ሊከፈት ሲል መንቀሳቀስ እስከማልችል ድረስ የህዝቡ ግፊያ ከምለው በላይ ሆኖ አገኘሁት። ሰውነቴን ከባድ የኤሌክትሪክ ሞገድ እንደያዘው ሰው አሁንም መርገፈገፉን አልተወም። ጂም እንዲህ አለኝ «ቤኒ በሩ ሲከፈት የቻልከውን ያህል ወደፊት ለመወርወር ሞክር» መልሼም «ለምን?» አልኩት ። «እንደዛ ካላደረግህ መጨረሻ ላይ ራስህን የምታገኘው መሬት ላይ በህዝብ ተረጋግጠህ ነው» አለኝ። ከዚህ በፊት በዚህ ስፍራ ላይ ተገኝቶ የገጠመውን ነገር ስለሚያውቅ ነበር ቢሊ በየዋህነት ይህን ምክር የመከረኝ። እኔ ግን ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲህ ያለ ግፊያ ይኖራል ብዬ አላሰብኩም። ያም ሆነ ይህ በሩ ወዲያው ተከፈተ። ምንም ማድረግ አልችልም። ብቻ ምን ዓይነት ሀይል እንዳገኘኝ አላወኩም። ባለ በሌለ ዓይሌ ልክ እንደ ኮከብ የኦሎምፒክ የሩጫ ተወዳዳሪ ወጣቱን ሆነ ሽማግሌውን፣ ጎልማሳውን ሆነ አዛውንቱን ጥሼ ራሴን ያገኘሁት የቤተክርስቲያኒቱ የመጀመሪያ ረድፍ ነበር። የዕለቱ ፕሮግራም አስተናባሪ ወደ ጆሮዬ ቀረብ አለና «ወንድም የመጀመሪያ ረድፍ ለተወሰኑ ሠዎች የተለየ ሥፍራ ነው» አለኝ። የአስተናጋጁ ንግግር የገባኝ ኋላ ነው። ካትሪን ኩልማን በአገልግሎቷ ወቅት ፊት ለፊቷ ማንም ሰው እንዲቀመጥ አትፈልግም። ለመንፈስ ቅዱስ አገልግሎትና እንቅስቃሴ እጅግ ጠንቃቃ ስለሆነች እፊት ለፊቷ እንዲሆኑ የምትፈቅደው የጸሎት ጓዶቿ ብሎም ለአገልግሎቷ አዎንታዊ አስተሳሰብ ያላቸው ቅዱሳኖች ብቻ ናቸው። ወደ እኔ ጉዳይ ስመጣ የዛን ዕለት ሰውነቴ ላይ እየተሰማኝ ካለው ቫይብሬተር ስሜት ጋር ደምሬ ከአስተናጋጁ ጋር አታካራ ውስጥ መግባት እንደሌለብኝ ተረዳሁ። በዚህ መካከል ሁለተኛው መስመር በሰዎች ተሞላ። ዳሩ ግን ሶሰተኛው መደዳ ባዶ ነበር። እፎይ ብለን እኔና ጂም ሶስተኛው ረድፍ ላይ ተቀመጥን። ዋናው ፕሮግራም ሊጀመር ገና አንድ ሰዓት ይፈልጋል። ስለዚህ በእጄ ላይ ያለውን ሙቀት ሰጪ ጓንት፣ ኮትና ቦቴ ጫማ አወላለቅሁኝ። ራሴን ፈታ ለማድረግ የበለጠ ስሞክር ያ ሰውነቴን የሚያረገፈግፈው ኃይል ጭራሽ እየባሰብኝ መጣ። ሊቆምልኝ አልቻለም። የሚያርገፈግፈኝ ኃይል እጄና እግሬ ውስጥ እየጨመረ መጣ። ልክ ከአንድ ዘመናዊ የኤልክትሪክ ማሽን ጋር የተጋጠምኩ ይመስላል። እንዲህ ያለው ስሜት ለእኔ ፈጽሞ እንግዳ ነበር። ከልቤ አውነቱን ስነግራችሁ ፍርሃት ያዘኝ። የኦርጋን ሙዚቃ ከመድረኩ አካባቢ መደመጥ ሲጀምርማ የባሰ ሰውነቴ ይረገፈገፍ ጀመር። ታዲያ ስሜቱ የህመምተኛ ስሜት አይደለም። የሆነ አለ አይደለም የጉንፋን ቫይረስ ሲይዛችሁ የሚሰማችሁ ስሜት አልነበረም። ቀስ በቀስ እንደውም ኃይሉ በሰውነቴ ላይ እየጨመረ ሲመጣ ስሜቱ ነፍሴንና መንፈሴን ደስ ያሰኝ ጀመረ። እንደውም እየቆየ ሲሄድ ልዩ የደስታ ምንጭ እየሆነልኝ መጣ። ሰውነቴ ላይ እየተገለጠ የነበረው ልዩ የሆነው ኃይል አካላዊ መሆኑ ቀርቶ መንፈሳዊ እንደሆነ እየገባኝ መጣ። ከዚህ በፊት በማላውቀው በዛ በረከት ውስጥ ሆኜ ካትሪን ኩልማን ከየት እንደመጣች አላውቅም። ቀና ስል መድረክ ላይ ቆማ አየኋት። በፍጥነት የጉባኤው አየር በእግዚአብሔር ህልውና ቻርጅ ሲሆን ይሰማል። ምን መጠበቅ እንዳለብኝ አላውቅም። ከዛ በኋላ ለሶስት ሰዓታት ያህል ሰውነቴ በከባድ የእግዚአብሔር ህልውና ሞገድ ያለማቋረጥ ሲርድ ነበር። ድምጽ የለም፤ የሰማይ መላእክት ዝማሬ የለም፤ በቃ ምንም ሃይማኖታዊ ክዋኔ አልነበረም። ብቻ አንድ ነገር ማድረጌን አስታውሳለሁ። ዝማሬ ሲጀመር በሁለት እግሮቼ ቆሜ፣ እጆቼን ወደ ሠማይ ከፍ አድርጌ እምባ ከዓይኖቼ እንደ ጅረት ያለማቋረጥ እየፈሰሰ አምላኬን ሰማየ ሰማያት ውስጥ ገብቼ ማምለኬን አስታውሳለሁ።
ጉባኤተኛው በሙሉ «እንዴት ታላቅ ነህ» የሚለውን ዝማሬ ይዘምራል። ልክ እንደ ቦምብ የፈነዳሁ ያህል ይሰማኝ ነበር። ከዚህ በፊት እንደዚህ እምባ ፈጥኖ ከዓይኔ ወጥቶ አያውቅም። በመንፈስ ሀሴት አድርጎ መጦዝ ታውቃላችሁ? እኔ ግን ከዛ በላይ በሆነ የመንፈስ ክብር ነበርሁ። የዛን ዕለት ሁለንተናዬ ሁሉ መዝሙር ሆነ ። በቃል ገልጬ ለመናገር ስሞክር «ነፍሴ ከፍ ባለ ግርማ ውስጥ ገብታ አዳኟን አመለከች» ብዬ ብናገር ስሜቴን በከፊል ይገልጥልኛል ብዬ አስባለሁ። በዚህ ክብር ውስጥ ገብቼ መዋኘት ስጀምር በሥጋዬ ላይ የነበረው የመርገፍገፍ ኃይል አቆመ። ያ የአምልኮ አውድ ግን አሁንም ቀጠለ። ፈጽሞ አላቆመም። የሆነ በንጠቀት ሥርዓት ያለሁኝ መሰለኝ። አድርጌው ከማውቀው በላዬን አዳኜን ፣ ኢየሱስ በሁለንተናዬ ምልዑ ክብር ገብቼ አመለኩት። ሌላው ፍጥረት ተሰምቶት ይሆን አይሁን እኔ አላውቅም። በዛ በለጋ የወጣትነት ዕድሜዬ፣ የዛን ዕለት አምላኬን አመለኩት። እግዚአብሔር ህይወቴን በአምልኮ መንፈስ ዳሰሰ። እንደዛ ቀን ሰማይና ምድርን የፈጠውን አሎሂን አምልኬ አላውቅም። ልክ እንደ ሞገድእዛው ቆሜ ሳለሁ ጌታዬን ማምለኬን አላቆምኩም። ዓይኔን ከፍቼ ዙሪያዬን አማትሬ ማየት ጀመርኩኝ። ድንገት ብርድ እንደ መታኝ ሰውነቴን ተሰማኝ። ከየትኛው አቅጣጫ እንደመጣ አላወቅሁም። ቀስ ያለና ረጋ ያለ ነው። ልክ እንደ ባህር ዳርቻ ንፋስ። ወደ ዛጉት የቤተክርስቲያኒቱ ህንጻዎች የመስኮት መስታወቶች ተመለከትሁ። ይሁን እንጂ ሁሉም ዝግ ናቸው። ደግሞም ክፍት ቢሆኑ እንኳን ከህንጻው ጣራ ጋር ከፍ ብለው የተሰሩ ስለሆነ የብርድ ምት ሊያመጡብኝ እንደማይችሉ አስተዋልሁ። እንዲህ ያለው ነፋስ አዘል ሞገድ አሁን እንግዳ ልምምዴ ነው። ከዚህ በፊት አጋጥሞኝ አያውቅም። ከአንዱ እጄ ወደ ሌላኛው እጄ እየተላለፈ ሲሄድ ተሰማኝ። አሁን ደግሞ ሰውነቴ ላይ ምን እየተካሄደ ነው ? ለሌላው ሰው እየተሰማኝ ያለውን ነገር ለመናገር ድፍረት ይኖረኝ ይሆን? እየተሰማኝ ያለውን ነገር ብነግራቸው አህይምሮዬን እንዳጣው አድርገው ይቆጥሩ ይሆናል ብዬም አሰብኩኝ። ቢያንስ ለአስር ደቂቃ ያህል እንደሞገድ በሰውነቴ ላይ የሚያልፈው ኃይል መላውን ማንነቴን አጠበኝ። አለ አይደል የሆነ ሰው ሰውነቴን በንጹህ ብርድ ልብስ ጠቅልሎ እንዳቀፈኝ ያህል ተሰማኝ። በዚህ መካከል ካትሪን ኩልማን አገልግሎቷን ቀጥላለች። በመንፈስ ተወስጄ ስለ ነበር በእርሷ አገልግሎት ውስጥ ተሳታፊ አልነበርኩም። ጌታ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ወደ እኔ የቀረበበት ደቂቃዎች ውስጥ ተውጬ ነበር። ከኢየሱሰ ጋር መነጋገር ፈለግሁ «ዳሩ ግን እናገር የነበረው ቃል በሹሹክታ ነበር። እርሱም እንዲህ የሚል ቃል «ውዴ ኢየሱስ እባክህን ማረኝ» ደግሜም አልኩት «ኢየሱስ ሆይ እባክህን በምህረትህ አስበኝ»። ታውቃላችሁ ራሴን እንደማይጠቅም ሰው ቆጠርኩት። ልክ ኢሳያስ ወደ እግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ገብቶ እንደተሰማው የበደለኝነት ስሜት እኔንም ተሰማኝ።
እኔም፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ (ኢሳ 6፡5) ።
እንዲሁ ሰዎች ኢየሱስ ሲያዩት የሚሰማቸው ስሜት ይህ ነው። ወዲያውኑ የሚታያቸው የእነርሱ ደካማ የህይወት ገጽታ ነው። ፍጹም ከበደልና ከሀጢያት ህይወት መንጻትን ይፈልጋሉ። እኔም ላይ የሆነው ጉዳይ ይህ ነው። መገኘቱ በክብር ወደ እኔ ሲመጣ የተሰማኝ ይኸው ነው። «ጌታ ኢየሱስ ሆይ ምህረትህ በእኔ ይግነን» ደጋግሜ አልኩኝ። ወዲያው የጌታን ድምጽ ሰማሁ። ያ ድምጽ የጌታ አንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩኝ። የረጋና ልስልስ ያለ ጨዋ ድምጽ ነበር። «ምህረቴ ለአንተ በቂ ነው» አለኝ። እስከዛን ዕለት ድረስ የእኔ የጸሎት ህይወት እንደ ማንኛውም ጤነኛ ክርስቲያን መካከለኛ ነበር። ያን ዕለት ግን በጸሎቴ ቃል ይወጣ የነበረው ከእኔ አንደበት ብቻ አልነበረም። በምላሹም የጌታን ድምጽ መስማት ቻልኩኝ። እኔ ብቻ ሳልሆን ውዴም ድምጹምን ያሰማኝ ጀመር።
እንዴት ያለ ህብረት መሰላችሁ? ፒተስበርግ ከተማ በመጀመሪያቱ የፕሪስባይቴሪያን ቤተክርስቲያን ውስጥ በሶስተኛ የመቀመጫ ረድፍ በእኔ ላይ የሆነው ነገር የወደፊት አገልግሎቴ ላይ ሊሆን ስላለው ግርማ የሞላበት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ጠቋሚ ትንቢታዊ ጉብኝት ነበር። እነዛ ቃላቶች ደጋግመው በጆሮዬ ላይ ያቃጭላሉ ፤ « ምህረቴ በቂህ ነው» በነበርኩበት ቦታ ተቀምጩ መጮህና ማልቀሴን ቀጠልኩኝ። በእነዛ ሠዓታቶች ውስጥ ከተሰማኝ ሥሜት በላይ ምንም ነገር ሊያሸነፈኝም ሆነ ሊበልጥብኝ አይችልም። የመንፈስ ቅዱስ ህልውና በክብር በእኔ ላይ ተገልጦ ማንነቴ ምልዑ ተጨባጭ ተሃድሶ ስላመጣ ከምንም ጋር ላወዳድረው አልችልም። የዛኑ ዕለት የኒኩሊየር ቦምብ ፒትስበርግ ውስጥ ፈንድቶ መላው አለም ቢጠፋ ግድ አይሰጠኝም። በዛን ጊዜ የተሰማኝ ደስታ ጳውሎስ ለፊሊጲስየስ ሰዎች በላከው ደብዳቤ ላይ የጻፈው መልእክት ብቻ ነው። ያለሁበትን የዛን ዕለት ቅጽበታዊ ማንነቴን የሚገልጥልኝ እርሱ ብቻ ነው። «አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል» (ፊሊ 4፡7)።
ወዳጄ ጂም የዛን ዕለት በካትሪን ኩልማን አገልግሎት ስለሆነው ተሃምራት ሁሉ አወጋኝ። እኔ ግን ምንም ምስክርነት መስጠት አልችልም። እዛው ቤተክርስቲያን ውስጥ የዛን ዕለት የሚስ ኩልማን አገልግሎት ተሳታፊ ብሆንም። ምክንያቱም የዛን ዕለት ለሶስት ሰዓታት ያህል መንፈስ ቅዱስ ወደራሱ አለም ወስዶኛልና። ጂም እንደነገረኝ ከሆኝ ካትሪን ኩልማን እያገለገለች መስማት የተሳናቸው ሰዎች ሰምተዋል፤አንዲት በተፈጥሮ ሽባ የነበረች ሴትዮከዊልቸር ላይ ዘላ ተነስታ ሮጣለች፤ በርከት ያሉ ሰዎች ከእባጭና ከአርትሪቲስ እና ከማይለቅ ራስ ምታት ነጻ ወጥዋል። የካትሪን አገልግሎት ሰፊና ረጅም ነበር። ዳሩ ግን አይጠገቤ ነበር። ሠዓታት እንዴት እንዳለፉ አይታወቅም። ለትችትና ለነቀፋ የመጡ ጋዜጠኞች ሳይቀሩ የአገልግሎቷን እውነተኛነት በሚዲያዎቻቸው የዛኑ ምሽት አቀርበዋል።
ካትሪን ኩልማን ለምን ታለቅሳለች?
የካትሪን አገልግሎት በቀጠለ ቁጥር በጸጥታ መጸለዩን ተያያዝኩት። ድንገት በአዳራሹ ውስጥ የነበረው እንቅስቃሴ ሁሉ በድንገት ቆመ። እንዲህ ብዬ በልቤ ጸለይኩኝ «እባክህ ጌታ ሆይ ይህ ፕሮግራም ወደ ፍጻሜ እንዳይመጣ» ብዬ ። ቀና ብዬ ስመለከት ካትሪን ኩልማን ፊቷንና ጭንቅላቷን በሁለት እጆቿ ሸፍና ጮክ ብላ ታለቅሳለች። እንዲህ በቀላሉ ታለቅሳለች አይገልጸውም። ስቅስቅ ብላ ድምጿን ከፍ አድርጋ መርዶ እንደ ሰማ ሰው ከዓይኖቿ የእምባ ጅረት ታፈሳለች። በአዳራሹ ውስጥ ይሰማ የነበረው የግራንድ ፒያኖ ደምጽ ረጭ አለ። አስተናጋጆቹ ባሉበት ቦታ በረዶ እንደ ነካው ውሃ ተኮማትረው ቆሙ። ወደ እኔ ቀልብ ስመጣ ካትሪን ስለምን እንደምታለቅስ ምክንያቱን አላውቅም። የትኛውም አገልጋይ መድረክ ላይ ቆሞ እንዲህ ሲያለቅስ አይቼ አላውቅም። ይህ ለእኔ እንግዳ የክርስትና ትዕይንት ነበር። ካትሪን ኩልማን ምንድን ነው ያስለቀሳት? ምክንያቱስ ምንድን ነው? እንደውም መጨረሻ ላይ የእርሷን የአገልግሎት አጋሮች ስጠይቅ «ኸረ በፍጹም እንዲህ ስታለቅስ አይተናት አናውቁም» እንዳሉኝ አስታውሳለው። ለደቂቃዎች ያህል ሚስ ኩልማን በልቅሶ ውስጥ ነበረች። ከዛ ወደ ኋላ ጭንቅላቷን ዘንበል አድርጋ ከፊት ለፊቴ መጥታ ቆመች። ዓይኖቿ የእሳት ነበልባል የሚተፉ ይመስላሉ። የዛን ቅጽበት ሉሲፈር እራሱ አጠገቧ ቢቆም በእስትንፋሷ ብቻ የምታጠፋው ይመስላል። እጅግ ጀግና በሆነ መንፈስ ጣቶቿን ወደ ህዝቡ ዘርግታ እንዲህ አለች «እባካችሁን ... እባካችሁን ... እባካችሁን መንፈስ ቅዱስን አታሳዝኑት» አለች። እንደገና ልመና በሞላት ድምጸት ልክ ወላጅ እናት የምትወደው ልጅ ሊገደልባት ባለ ጊዜ የምታሰማውን ድምጸት ይዛ «እባካችሁን ... እባካችሁን ... እባካችሁን መንፈስ ቅዱስን አታሳዝኑት» አለች። እስካሁን ድረስ ያ የሚስ ኩልማን የፊት ገጽታ ይታወሰኛል። እስካሁንም በእነዛ ዓይኖቿ የምታየኝ ይመስለኛል። በዚህ ንግግሯ ምክንያት ከወረደብኝ ፈሪሃ መንፈስ ቅዱስ የተነሳ በአተነፋፈስ ስርዓቴ ላይ ሳይቀር እንኳን መንፈስ ቅዱስን እንዳላሳዝን እያልሁ እፈራ ጀመር።

በዚህ ሀሳብ ውስጥ ተውጬ ሳለሁ አሁንም ሚስ ኩልማን እንዲህ ስትል ተናገረች ፤ «ወገኖች አልገባችሁም? በህይወቴ አለኝ የምለው እርሱ ብቻ ነው ! » አሁን ግን በዚህ ንግግሯ መደነቅ ሞላብኝ «ምን እያለች ነው?» አልሁ። አሁንም በልመና ድምጽ ንግግሯን ቀጠለች። «እባካችሁን መንፈስ ቅዱስን አታቁስሉት። የቀረኝ፣ አለኝ የምለው ወዳጄ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። የምወደውን እርሱን አታቁስሉብኝ» አለች ። እነዚህ የሚስ ኩልማን ንግግሮች በልቤ ውስጥ ተሰንቅረው ቀሩ። እነዚህን ቃላቶች ስትናገር ከውስጧ ይወጣ የነበረው እስትንፋስ ሞገድ እንዴት እንደነበሩ መግለጥ አልችልም። ከዚህ በፊት እኛ ቤተክርስቲያን መጋቢው ስለ መንፈስ ቅዱስ ደጋግሞ አስተምሮናል። ግን እንዲህ ባለ እውነተኛ ስሜት አልነበረም። ብዙ ጊዜ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በዝርዝር አስተምሮናል። ግን እንደ ሚስ ኩልማን የግል ወዳጁ አድርጎ አይደለም። ሚስ ኩልማን ስትናገር እኮ እኔና እናንተ የምናውቀውን መንፈስ ቅዱስ እጅግ የቅርብ ጌታዋና ገዢዋ አድርጋ ነው።
ከዛ በኋላ ሚስ ኩልማን ረጅም ጣቷን ወደ እኔ ጠቁማ ግልጽ በሆነ ቋንቋ እንዲህ አለቺኝ። «ወንድሜ ከምንም ነገር በላይ በዚህ ምድር ላይ ያንተ ብቸኛ ወዳጅ መንፈስ ቅዱስ ነው» አለቺኝ። ልክ እየተናገረቺኝ መንፈስ ቅዱስ ሁለንተናዬን ተቆጣጠረው። ግነት በሌለበት ንጹህ ቋንቋ ስናገር መለኮታዊ እጅ ውስጤን በሙሉ ሲይዘኝ ተሰማኝ። እንዲህ እያልኩኝ ጮክ ብዬ በጉባኤ መካከል መናገሬን ቀጠልኩኝ « ይህንን ማግኘት ነበረብኝ፣ ይህንን ማግኘት ነበረብኝ .. ይህንን ማግኘት ነበረብኝ» ። እውነቱን ስናገር ሁሉም ጉባኤተኛ ልክ እንደኔው በዚህ ክብር ውስጥ ያለ መስሎኝ ነበር። ዳሩ ግን እኔ እንደማስበው አይደለም። እግዚአብሔር አምላካችን ለካ የግል አምላክ ነው !

እስከዛሬ ድረስ ያ የካትሪን ኩልማን አገልግሎት ለእኔ ብቻ የተዘጋጀ መንፈሳዊ ፕሮግራም እንደሆነ ይሰማኛል። እንደምትረዱኝ አምናለው። ያ ፕሮግራም ለምን እንደተዘጋጀ ሁሉ እምብዛም እውቀቱ የለኝም። በዛን ጊዜ ገና አዲስ አማኝ ነበርኩና። በውስጥ ህልውናዬ ውስጥ የተገለጠውን የሰማይ አለም መገኘት ግን መካድ አልችልም። ፕሮግራሙ ሊደመደም ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀረው መድረክ ላይ ቆማ ወደምታገለግለው ወንጌላዊት በአጽንኦት ተመለከትሁ። ዙሪያዋን በከበባት ደመና ተባርኬና ተማርኬ ደጋግሜ አየሁዋት። በመጀመሪያ አካባቢ የገዛ ዓይኖቼ እያፌዙብኝ እንዳለ ተሰምቶኝ ነበር። ይሁን እንጂ እይታዬ እውን ነበር። ገጽታ ፊቷ ልክ እንደ ጸሐይ ብርሃን ከደመናው ውስጥ እያፈተለከ ያንጸባርቃል። በእርግጥ እግዚአሔር ስጋ ለባሽ በሆነቺው እህት ላይ ይህን ክብር ያደረገው እርሱዋን ለማግነን አስቦ እንዳልሆነ አውቃለው። የኃይሉን ታላቅነት ለእኔው ለጋ ለሆነው ማንነቴ ያስረዳኝ ዘንድ ይህን እንዳረገ አውቃለሁ።
ፕሮግራሙ ልክ እንደተጠናቀቀ ጉባኤተኛው በሙሉ ከቤተክርስቲያኒቱ አዳራሽ ውስጥ ድንገት ንቅል ብሎ ወጣ። እኔ ግን ከተቀመጥኩበት ስፍራ መንቀሳቀስ አልቻልኩም። የሆነብኝን በሙሉ መልሼና መላልሼ መዘከር ብሎም መተግበር ከልቤ ፈልግሁኝ። በዛ ህንጻ ውስጥ የሆነብኝን በሙሉ በራሴ ጥረት ዝንተ ዓለም ብሮጥ እንደማላመጣው ገብቶኛል። ተመልሼ እዛው አክራሪ የይሁዲ፣ የካቶሊክና የግሪክ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ወደ ሆኑት ቤተሰቦቼ ጋ ስመለስ የበረታ ሰልፍ እንደሚጠብቀኝ አውቃለሁ። ከዛም በላይ ስለ ራሴ ያለኝ ምልከታ እጅግ የወረደ ነው። ምክንያቱም አንደበቴ የበዛ ኮልታፋ ስለሆነ የሰው ሁሉ መቀለጃና ማሾፊያ ነኝ። ከዚህ የተነሳ በልጅነት ዕድሜ እማርበት ከነበረው የካቶሊክ ትምህርት ቤት ውስጥ በኮልታፋ አንደበቴ ምክንያት ከፍተኛ መገለል ደርሶብኛል። ክርስቲያን ከሆንኩኝ በኋላ በዚህ ኮልታፋ አንደበቴ ምክንያት ብዙ ወዳጆች ማፍራት አልቻልኩም። ታዲያ እንዴት ነው አዳዲስ ሰዎችን አግኝቼ ለክርስቶስ ወንጌል መማረክ የምችለው ? የፈለገው ይምጣ ታሪክ ቀያሪ ከሆነው የፒትስበርግ የመንፈስ ቅዱስ መገኘት ውስጥ በፍጹም መውጣት አልፈልግም። በፍጹም ከእርሱ መገኘት ውስጥ ወጥቼ ከዚህ አለም አስጨናቂ የህይወት ገጽታ ጋር ህብረት ማድረግ አልፈልግም፡፡ ያለ መንፈስ ቅዱስ ሞገስ የለኝም፤ ያለ መንፈስ ቅዱስ አንደበቴ በቅጡ መናገር አይችልም፤ ያለ መንፈስ ቅዱስ በሰው ዘንድ ተቀባይነት አይኖረኝም፤ ያለ መንፈስ ቅዱስ …

Good Morning Holy Spirit
ትርጉም ሐዋሪያው እንዳለ በሽር

75 days Asere or Natanan Yabets Thanks to God
25/04/2022

75 days Asere or Natanan Yabets Thanks to God

75 days Asere or natanan yabets Thanks to God
25/04/2022

75 days Asere or natanan yabets Thanks to God

24/04/2022
24/04/2022

ዘጸአት 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ በዚህም ወር እስከ አሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቁት፤ የእስራኤልም ማኅበር ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት።
⁷ ከደሙም ወስደው በሚበሉበት ቤት ሁለቱን መቃንና ጉበኑን ይቅቡት።
⁸ በእሳት የተጠበሰውን ሥጋውንና ቂጣውን እንጀራ በዚያች ሌሊት ይብሉ፤ ከመራራ ቅጠል ጋር ይበሉታል።
⁹ ጥሬውን በውኃም የበሰለውን አትብሉ፥ ነገር ግን ከራሱ ከጭኑ ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት የተጠበሰውን ብሉት።
¹⁰ ከእርሱም እስከ ጥዋት አንዳች አታስቀሩ፤ እስከ ጥዋትም የቀረውን በእሳት አቃጥሉት።
¹¹ ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ፥ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ እንዲህ ብሉት፥ ፈጥናችሁም ትበሉታላችሁ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው።

22/04/2022

ጌታችን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለ6 ሰዓታት ቆይቷል።ሚስማር አይደለም ድንኳን የምንወጥረበት አይነት ትልቅ ችንካር በእጆቹ ላይ እግሮቹ ላይ የተመታው፣ በመስቀል ላይ ሆኖ ክብደቱን ሲለቀው እጆቹ ላይ የሚፈጠረው ህመም ከባድ ነበር።ቀና ለማለት ክብደቱን እግሩ ላይ ማድረግ አለበት ያን ጊዜ የሚፈጠረውን ህመም አስቡት ስቃዩ በጣም በጣም ዘግናኝ ነው።ይሄ ብቻ አይደለም መስቀል ላይ ያለ ሰው መናገር ከባድ ነው ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ 7 ነገሮችን ተናግሯል።ከእነዚህ ውስጥ አንዱ እና የመጨረሻው ተፈፀመ የሚል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ከስድስት የተለያዩ ቁስለቶች ደም ይፈሰው ነበር።ጌታ ኢየሱስ የሞተው ሞት የድል ሞት ነው ምክንያቱም በሞቱ ነው ድል የነሳው።
በታላቅ ድምጽ ጮኾ ነፍሱን ሰጠ፣ ሰው ሲሞት ጮኾ መሞት አይችልም፣ በታላቅ ድምጽ ለመሞት ኃይል ፣አቅም ይጠይቃል።ምክንያቱም ነፍሱን ተወስዶበት ሳይሆን በፍቃዱ ነው።ተፈፀመ አለ ምንድን ነው የተፈፀመው?
1)የኃጢያትን ችግር፣ውስብስብነት ካልተረዳን በቀር ኢየሱስ የከፈለልን ዋጋ አናውቀውም።የኃጢያትን ችግር ከሰው ይልቅ ፣ ከሰይጣን ይልቅ እግዚአብሔር ጋር ነው።እንዴት? እግዚአብሔር አጥብቆ የሚወደውን ሰው እና እግዚአብሔር አምርሮ የሚጠላው ኃጢያት ተገጣጠሙበት፣ መለየት እስከማይቻል ድረስ...ሰረፀ...ገባ ...መለየት በማይቻል መጠን ስለዚህ እግዚአብሔር በፅድቅ ፣በእውነት ፈርዶ የሰው ልጅ የሚገባውን ቅጣት በገሃነም መስጠት ይችላል ምንም ችግር የለበትም ግን ምህረቱ አይፈቅድለትም አምረሮ የሚጠላው ኃጢያት እንዲቀጣለት ቢፈልግም አጥብቆ የሚወደው ሰው ልጅ እንዲጠፋ አይፈልግም። እውነቱ ደግሞ የሰው ልጅ ምህረት ይደረግለት ፣ ዝም ብሎ ይዳን ፣ የዘላለም ህይወት ያገኝ ቢል ደግሞ ኃጢያት የሚገባውን ቅጣት ሳገኝ ፅድቁ እሺ አይለውም።መስቀል የእግዚአብሔእር ጥበብ እውነት እና ምህረትን ያስታረቀ ያስማማ ነው።ለመለኮታዊ ተግዳሮት መለኮታዊ መፍትሔ ያገኘበት ቦታ ነው መስቀል።
አጥብቆ የሚጠላውን ኃጢያት ልጁ ላይ አደረገ። ሮሜ 8፡3-4 ኃጢያትን በልጁ አደረገ እና ኃጢያትን ኮነነው።እግዚአብሔር በሰው ሁሉ ላይ ያለውን ቁጣ በልጁ ላይ አደረገ፣ ኃጢያትን ቀጣው፣ ኮነነ ያንን ጊዜ ፅድቁ ረካ እውነቱ ረካ ምክንያቱም ፍትህ ተፈፀመ።በመስቀሉ ስራ የሰው ልጅ አምኖ የሚድንበት ስራ ተሰራ።ኢየሱስ ራሱን ያቀረበው ለአብ ነው (ኤፌሶን 5:2) ለአብ ራሱን መስዋት አድርጎ አቀረበ።ኢየሱስ ክርስቶስ በፍፁም ቅዱስ ስለሆነ ያቀረበው መስዋት እንከን የሌለበት ነው እንደዚህ አይነት መስዋት ማቅረብ የሚችል የለም። አሁንም በዚህ መድኃኒት ወደ አብ የሚመጣ ሁሉ ተፈፅሞለታል፣ ተሰርቶለታል ሰተት ብሎ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት ነው ፣ አማላጅ አያስፈልገው፣ አጋፋሪ አያስፈልገው፣ ሰተት ብሎ መግባት ይችላል።
ኤፌሶን 2:16-18"ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።
“መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤
በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና"
የመስቀሉ ስራ ለሚያምን ሁሉ ፃዲቅ ያደርጋል። የኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነፃል።ተፈፀመ።
ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን

23/02/2022

የመልዕክቴ ርዕስ፦ (ጩህ!!) የሚል ነው፡፡

በጣም ተማረህ ታውቃለህ?? ከልብህስ አዝነህ ታውቃለህ?? እና ምሬትክ "'ኡኡኡ' ብለህ ጩህ" ብሎህ ያውቃል?? ስለዚህ ያ ስሜት ትክክለኛ ነው!! አትጥላው፡፡ ግን ለዚያ ስሜት ተገቢ መልስ መስጠት አለብክ፡፡ መጮኽ አለብክ፡፡ ነግር ግን የምትጮኸው የትና ወደ ማን እንደሆነ በግልጽ ጠንቅቀህ ማወቅ ይኖርብሃል። ብቻህን ወደጫካ ገብተክ "ኡኡኡ" ካልክ ለጊዜው ብቻ ጭንቀትክ ይቀልልክ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ወደ መኖሪያ ስፍራክ ስትመለስ፡፡ ጭንቀትህ ተመልሶ ይመጣል። ሰው ባለበት በመኖሪያህና በስራ ቦታህ ብትጮህ ደግሞ ሰው ትረብሻለክ እንጂ መፍትሔ አታመጣም፡፡ ከጭንቀትህ የተነሳ መጮህክኮ ስህተት አልነበረም። ስህተት የሆነው የጮህክበት ቦታ ነው። ጴጥሮስን አስታውስ?? ደቀመዛሙርቱና ኢየሱስ በጀልባ ወደ ማዶ ወደ (ጌርጌሴኖን) እየተሻገሩ በነበረ ጊዜ ወጀቡን አየና እንዳይሰጥሙ ፈርቶ "ጌ...ታ ሆይይይ ጌ....ታ ሆይይይይይ ልንጠፋ ነው" ብሎ ወደ አምላኩ እንደጮኸ አስታወስክ? ጌታ ተነስቶ ማዕበሉን ጸጥ አደረገው፡፡ ክብር ለስሙ ይሁን፡፡ ዛሬ ከሰማከኝ እኔ እንዲህ ብዬ እመክርሃለሁ መጮህክ ካልቀረ ሰምቶ ወደሚመልሰው፡፡ ጆሮዎቹን ወደ ጩኸትክ ወደሚልከው፣ አይኖቹን በአተኩሮት ልኮ ወደ አንተ ወደሚመለከተው፣ አፅናኝ ድምጹንም ወደሚልከው፡፡ ወደ እግዚአብሔር ጩኽ፡፡ እሱን ጩኸትክ አይረብሸውም፡፡ ይልቁንም ለጩኸትህ ያዝናል፡፡ ምላሽም ይሰጣል ምክንያቱም እውነተኛ አባት ነውና። ጌታ በቃሉ እንዲህ ይላል፡፡

" ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ። "
(ትንቢተ ኤርምያስ 33:3)

ስለዚህ ሁላችንም በየግላችን በየቋታችን ወደ አምላክ እግዚአብሔር እንጩኽ። ስለ ህይወታችን፣ ስለ ቤተክርስቲያን፣ ስለ አገራችን እንጩህ፡፡ ስላልዳኑ ሰዎች እንጩህ፡፡ በአጠቃላይ ጭንቀታችንን ሁሉ እንጩህ፡፡ ነገር ግን ጩኸታችን እንዲሰማ የምንጮኸው ወደ ሰውና ወደ ባዶ ቦታ፡ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር ብቻ ይሁን ተባረኩልኝ፡፡

Address

Adama

Telephone

+251911492476

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yabets posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yabets:

Shortcuts

Share