Chazma Asel Real Estate S.C

Chazma Asel Real Estate S.C ጫዝማ አሠል ሪል እስቴት አክስዮን ማህበር
ውንጌት አከባቢ 4040 ካሬ መሬት ከባለ ይዞታ በመግዛት 2B+G+12 የሆነ አራት ብሎክ ያለው አፓርትመንት በመገንባት ላይ ይገኛል።

15/08/2026

Hello everyone!

በባንክ ብድር አማራጮች ዙርያ ከዳሸን ባንክ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።     ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከዳሽን ባንክ ጋር ከወለድ ነፃ በሆነ የብድር አማራጮች ዙሪያ ሠፋ ያለ የሁለት...
22/07/2026

በባንክ ብድር አማራጮች ዙርያ ከዳሸን ባንክ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።

ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከዳሽን ባንክ ጋር ከወለድ ነፃ በሆነ የብድር አማራጮች ዙሪያ ሠፋ ያለ የሁለትዮሽ ወይይት ተካሄደ።

የጫዝማ አሰል ሪል እስቴት አ.ማ የፋይናንስ አማራጮቹን ይበልጥ ለማስፋት ከዳሽን ባንክ የስራ ሃላፊዎች ጋር ቀጣይ በሚተገበሩ ከወለድ ነፃ በሆነ የባንክ ብድርና የፋይናንስ አማራጮች ዙሪያ በትናትናው ዕለት በድርጅታችን ዋና መሥሪያ ቤት ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱም የዳሸን ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የጫዝማ አሰል ሪል እስቴት አ.ማ አመራሮችና የተቆጣጣሪ ቦርድ የተገኙ ሲሆን በዋናነት ድርጅቱ በዊንጌት አካባቢ የሚያስገነባቸው ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንቶች በፍጥነት ለማጠናቀቅ የሚቀርቡ ከወለድ ነፃ የሆነ የብድር አማራጮችን ማመቻቸት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።

የባንኩ አመራሮች ባንካቸው ከወቅታዊ የገበያ ሁኔታዎች ጋር የተጣጣሙ እና ሂደታቸው ፈጣን ከሆኑ የብድር አማራጮች ውስጥ ከእኛ ድርጅት አመሰራረት እና የፋይናንስ አሰባሰብ አንጻር የተሻሉ የሚባሉ የብድር ስልቶች ዙርያ ማብራርያ አቅርበዋል። የጫዝማ አሰል ሪል እስቴት አመራሮች በበኩላቸው ባንኩ ላሳየው ዝግጁነት ምስጋና አቅርበው ይህ የባንክ አማራጭ በሂደት ላይ ያለው ግንባታ ቶሎ በማጠናቀቅ አባላቱ በአጭር ጊዜ ቤቱን እንዲረከብ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም የባንኩ አመራሮች አሁን ላይ ግንባታዎቹ ያሉበት ደረጃ ሳይት ሄደው ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ስምምነቱ ለመፈጸም በቀጣይ በባንኩም ሆነ በድርጅታችን በኩል መሟላት ያለባቸው ዝርዝር ጉዳዮች በመለየት ክትትል እንዲደረግባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል እንዲሁም ይህንኑ ከወለድ ነፃ የሆነ የብድር አማራጮችን ለመተግበር በተለይ የዚህ አመቱ መጨረሻ ላይ አክስዮን ማህበሩ ካሉት አባላቶች መካከል ሙሉ ለሙሉ የሚጠበቅባቸውን ዕዳ ለከፈሉና ጥሩ የአከፋፈል አፈፃፀም ላሳዩ አባላት ብቻ ታሳቢ ያደረገ ሆኑንም በውይይቱ ተመላክቷል።

Address

Addis Ababa
MULUGETAABATEPARK

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Chazma Asel Real Estate S.C posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category